Aller au contenu principal

page search

Bibliothèque በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረቱ በአገር አቀፍ የምግብ ዋስትና ማእቀፍ ውስጥ የመሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብት ይዞታ መብት በኃላፊነት ማስተዳደርን የተመለከቱ መመሪያዎች

በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረቱ በአገር አቀፍ የምግብ ዋስትና ማእቀፍ ውስጥ የመሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብት ይዞታ መብት በኃላፊነት ማስተዳደርን የተመለከቱ መመሪያዎች

በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረቱ በአገር አቀፍ የምግብ ዋስትና ማእቀፍ ውስጥ የመሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብት ይዞታ መብት በኃላፊነት ማስተዳደርን የተመለከቱ መመሪያዎች
ይህ መመሪያ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የመሬት፤ ዓሣ እና ደን አስተዳዳርና ጥበቃ፤ ለብሄራዊ የምግብ ዋስትና በሚል ተዘጋጅቶ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ነው፡፡

Resource information

Date of publication
Avril 2019
Resource Language
ISBN / Resource ID
ISBN 978-92-5-131438-8
Pages
46
License of the resource

የነዚህ የበጎ ፈቃድ መመሪያዎች አላማ የመሬት፣ የአሳ እንዲሁም የደን ይዞታ አስተዳደርን ለማሻሻል ምሪት መስጠት ብሎም እንደማጣቀሻ ማገልገል ሲሆን ይህም ለሁሉም ሰው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የተሰኘው መርሆን መሠረት ያደረገ እና የሰው ልጆችን በቂ ምግብ የማግኘት መብት በአገር አቀፍ የምግብ ዋስትና ማዕቀፍ ውስጥ በዘላቂነት እውን እንዲሆን ድጋፍ መስጠት ነው። የነዚህ መመሪያዎች አላማ ረሃብን እና ድህነትን ለማጥፋት ለሚደረገው አለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ርብርብ አስተዋጽዖ ማድረግ ሲሆን ይኸውም ቀጣይነት ያለው የመሬት ልማት ለዕድገት መሠረታዊ ጉዳይ ነው የተሰኘውን መርሆ በማንገብ ፍትሃዊ የመሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብት ክፍፍል እንዲሁም ዋስትና ያለው የይዞታ መብት እንዲኖር ማስተዋወቅን ይጨምራል። ድህነትን እና ረሃብን ማጥፋት እንዲሁም ቀጣይነት ያለው የተፈጠሮ ሀብት አጠቃቀምን ማስፈን በዋናነት የማህበረሰቡን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን መሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብቶች ማግኘት ላይ የተመሠረተ ነው። የአብዛኛው በተለይ የገጠሩ ድሃ ህዝብ መተዳደሪያ ሙሉለሙሉ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የእነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች ባለይዞታ መሆን፣ መወሰን እና ዋስትና ማግኘት ላይ የተመሠረተ ነው። እነዚሁ የተፈጥሮ ሀብቶች የምግብ እና የመጠለያ አገልግሎት ከመሰጠት ባሻገር የማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ሀይማኖታዊ መሠረቶች ናቸው፤ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ፋይዳቸውም የትየለሌ ነው። የመሬት፣ የአሳ እንዲሁም የደን ይዞታ ሀላፊነት በተሞላ መንገድ ማስተዳደር ከሌሎች እንደ ውሀ እና ማዕድን የመሳሰሉ የተፈጠሮ ሀብቶች ማግኘትና አስተዳደር ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑ አሌ የማይባል ሀቅ ነው። ሃገራት እነዚህን የተፈጥሮ ሀብቶች የሚያስተዳድሩበት የተለያዩ ዘዴዎች እና ሥርዓቶች እንዳላቸው ስለሚታወቅ፣ ይህ መመሪያ እንደ ተገቢነቱ ከየሀገራቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ሊተገብሩት ይችላሉ። ህዝቦች፣ ማህበረሰቡ እና ሌሎች አካላት የመሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብት ባለይዞታ እንዴት እንደሚሆኑ የሚወሰነው እና ቁጥጥር የሚደረገው ማህበረሰቡ በዘረጋው የይዞታ አስተዳደር ሥርዓቶች ነው። እነዚህ የይዞታ አሰተዳደር ሥርዓቶች ማን የትኛውን የተፈጥሮ ሀብት ለምን ያህል ጊዜ እና በምን ዓይነት ሁኔታዎች መጠቀም አንደሚችል ምሪት ይሰጣሉ። የይዞታ አሰተዳደር ሥርዓቶቹ የተፃፉ ሕጎች እና ፖሊሲዎችን አሊያም ያልተፃፉ ባህላዊ ልምዶችን መሠረት ያደረጉ ሊሆኑ ይችላሉ። የይዞታ አስተዳደር ሥርዓቶች ከአለም ህዝብ ብዛት መጨመር ጋር ተያይዞ በጨመረው የምግብ ፍላጎትእንዲሁም ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከተፈጠሮ ሀብት ውድመት የተነሳ በቀነሰው የመሬት የአሳ እና የደን መመናመን ከፍተኘ ጫና እየደረሰባቸው ነው። ደካማ እና ዋሰትና የሌላቸው የይዞታ መብቶች ቀድሞ የነበረውን የህዝቡን ለረሀብ እና ለድህነት ተጋላጭነት ከማባባሱም ባሻገር ተጠቃሚዎች በሚያደርጉት እሽቅድምድም የፀብ እና የተፈጥሮ ሀብት መመናመን ምክንያት ሊሆንም ይችላል።

የይዞታ አስተዳደር ሥርዓት ህዝቦች፣ ማህበረሰቦች እና ሌሎችም አካላት የይዞታ መብት ይኑራቸው አይኑራቸው፣ ከሌላቸውስ እንዴት የመብት ባለቤቶች ይሁኑ እንዴትስ የመሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብት መብታቸውን አውቀው ተያያዥ ግዴታቸውንም ይወጡ የሚሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ወሳኝ አካል ነው፡፡ ብዙ የይዞታ ችግሮች ከደካማ የይዞታ አስተዳደር የተነሳ ይከሰታሉ፡፡ የአስተዳደር ጥንካሬ የይዞታ ችግሮች ከተከሰቱም በኋላ እንኳን መፍትሄ ለመሻት ወሳኝ ነው፡፡ ደካማ አስተዳደር ማህበራዊ መረጋጋትን፣ እና ለዘለቄታው በሚበጅ መልኩ የሚደረግን የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እንዲሁም ኢንቨስትመንትን እና የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል፡፡ ብልሹ አሰራሮች ከነገሱ ወይም ፈፃሚ አካላት የባለ ይዞታዎችን መብት ለማስከበር አቅም ካጡ ህዝቦች የቤት፣ የመሬት፣ የአሳ፣ የደን እንዲሁም የመተዳደሪያ ይዞታዎቻቸውን ሁሉ ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ደካማ አስተዳደር በሚፈጥራቸው ግጭቶች ሰዎች ህይወታቸውን ጭምር ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ሀላፊነት የተሞላ የይዞታ አስተዳደር ሥርዓት ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የተረጋጋ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ከማምጣቱም ባሻገር ድህነትን እና የምግብ ዋስትና ችግርን በማስወገድ ኃላፊነት የተሞላው ኢንቨስትመንትንም ያበረታታል፡፡

እያደገና እየሰፋ ለመጣው የይዞታ አስተዳደር ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት እና አጋሮቹ ኃላፊነት የተሞላው የይዞታ አስተዳደር መመሪያ የማዘጋጀት ሥራ ጀመሩ፡፡ ይህ እንቅስቃሴ መሠረቱ ያደረገው እና የሚደግፈው በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ እና በአገራዊ ማዕቀፍ ውስጥ ያለ ቀጣይነት ያለው በቂ ምግብ የማግኘትን መብት (በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ምግብ የማግኘት መብት መርሆዎች) ሲሆን ይህም የተባበሩት መንግሠታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት 127ኛ ጉባኤ በህዳር 2004 እና በ2006 የአለም አቀፉ የግብርና ማሻሻያ እና የገጠር ልማት ኮንፍረንስ (ICARRD) በተደረጉበት ጊዜያት የፀደቁ ናቸው፡፡

የአለም የምግብ ዋስትና ኮሚቴ (CFS) ጥቅምት 2010 ባደረገው 36ተኛው ጉባኤው መመሪያው ሁሉን አቀፍ እንዲሆኑ እና የመጀመሪያውም ረቂቅ ፅሁፍ ኮሚቴው ለሚያደርገው ግምገማ ክፍት እንዲሆን አበረታትቷል፡፡ ይህንኑ ለማስፈፀም ኮሚቴው ረቂቁን የሚገመግም ቡድን ለማቋቋም ወስኗል። እነዚህ መመሪያዎች የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት ያዘጋጃቸውን ሌሎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረቱ መርሆዎችን እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን ያገኙ ደረጃዎችን እና ኃላፊነት የተሞሉ አፈፃፀሞችን ተከትለው የተዘጋጁ መመሪያዎችን መሠረት አድርገው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ይህ መመሪያ መሠረት ካደረጋቸው መመሪያዎች መካከል፡ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ምግብ የማግኘት መብት መርሆዎች፣ ሀላፊነት የተሞላ የአሳ ማስገር ደንብ፣ የተባይ ማጥፊያ ስርጭት እና አጠቃቀም አለም አቀፍ ደንብ፣ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ፣ ኃላፊነት የተሞላ የተተከሉ ደኖች አስተዳደር መመሪያ እንዲሁም የእሳት አደጋ መከላከያ በፈቃደኝነተ ላይ የተመሠረቱ መመሪያዎች፣ መርሆዎች እና እስትራቴጂዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህ መመሪያዎች በአንፃራዊነት አጭር ሲሆኑ እስትራቴጂዎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ሕጎችን፣ መርሀ-ግብሮችን፣ ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ለማዘጋጀትና መዋቅሮችን ለመስራት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ መመሪያዎቹ ከሌሎች ተጨማሪ ጽሁፎች ጋር የሚገኙ ሲሆን እነርሱም አስፈላጊ ሲሆን በአንድ ጉዳይ ላይ ዝርዝር ቴክኒካዊ መረጃዎችን፣ ስልጠናዎችን፣ ድጋፎችን እና ለአፈፃፀም የሚረዱ ተጨማሪ ምሪቶችን የሚሰጡ ናቸው፡፡ እነዚህ መመሪያዎች ግንቦት 11 20012 በተካሄደው በአለም የምግብ ዋስትና ኮሚቴ 38ተኛው ልዩ ጉባኤ ላይ የጸደቁ ናቸው፡፡

የተዘጋጁት በቡድን ሲሆን ይኸውም በሰኔ፣ ሀምሌ እና ጥቅምት 2011 እንዲሁም መጋቢት 2012 በነበሩት የቡድኑ ጉባኤዎች ነው፡፡ ዝግጅቱ የተደረገው በ2009 እና 2010 በተደረገ ሁሉን አቀፍ በሆነ የምክክር መድረክ ነው፡፡ ክልላዊ ምክክሮች በብራዚል፣ በቡርኪናፋሶ፣ በኢትዮጵያ፣ በዮረዳኖስ፣ በናሚቢያ፣ በፓናማ፣ በሮማኒያ፣ በሩሲያ ፌደሬሽን፣በሳሞዋ እና በቬትናም ተደርገዋል፡፡ እነዚህ ክልላዊ ምክክሮች ከ133 አገራት ወደ 700 ሰዎችን ያሳተፉ ሲሆን እነርሱም የመንግሥትና የግሉን ዘርፍ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ወክለው የተገኙ ናቸው፡፡ አራት የምክክር መድረኮች በተለይ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተዘጋጁ ሲሆን እነርሱም የአፍሪካ ማሊ፣ የእስያ ማሌዢያ፣ የአውሮፓ እንዲሁም የመካከለኛው እና የምእራብ እስያ ጣሊያን እና የላቲን አሜሪካው ደግሞ ብራዚል ውስጥ ሲደረጉ 200 ሰዎችን ከ70 አገራት አሳትፎ ተጨማሪ ደግሞ ከግሉ ዘርፍ 70 ተሳታፊዎችን ከ21 አገራት እንዲታደሙ ሆነዋል፡፡ እነዚህ መመሪያዎች በኤሌክትሮኒክ ምክክር ጊዜ የቀረቡ ፕሮፖዛሎችን እና ዜሮ ድራፍቶችን ይዘዋል፡፡ ዜሮ ድራፍቶቹ እንዲሻሻሉ በመንግሥት እና በግል ዘርፎች፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም

ከመላው አለም ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡ እነዚህ መመሪያዎች ከአለም አቀፍ እና ከክልል መመሪያዎች ላይ የተወሰዱ እንዲሁም አብረው የሚሄዱ ሲሆን ይህም የሰው ልጆች መብት እና የይዞታ መብትን በተመለከተ ከሚሊኒየሙ የዕድገት ግቦችም ላይ የወሰዳቸውን መርሆዎች ይጨምራል፡፡ የነዚህ መመሪያዎች አንባቢዎች የይዞታ አስተዳደርን ማሻሻል በሚፈልጉ ጊዜ ግዴታዎቻቸውን መፈፀም በሚያስችላቸው መልኩ በመደበኛ ሁኔታ እንዲገመግሙ እና በፈቃደኝነት ተጨማ ሪ ምሪት እንዲጠይቁ ይበረታታል ፡፡

Share on RLBI navigator
NO